August 5, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን በመወከል በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና በመሳተፍ ወደ አንደኛ ሊግ ያደገው የቴፒ ከተማ የወንዶች እግር ኳስ ክለብ በቴፒ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

‎በኢትዮጵያ ክለቦች ሻምፒዮና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን ፣ሸካ ዞንንና ቴፒ ከተማን በመወከል በድረዳዋ በተካሄደው ውድድር 8ቱ ውስጥ በመካተት ወደ ኢትዮ ሊግ 1 መግባቱን ያረጋገጠው የቴፒ ከተማ ወንዶች እግር ኳስ ቡድን በቴፒ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

‎የቴፒ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደመላሽ ገዳ በወቅቱ እንዳሉት
ስፓርት መዝናኛና የኢኮኖሚ ምንጭ ከመሆን አልፎ ፍቅርና አንድነትን በሕዝቦች ዘንድ የሚያጎለብት መሳሪያ መሆኑን ገልፀው የቴፒ እግር ኳስ  ክለብ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም ላስመዘገበው ውጤት ምስጋና አቅርበዋል።

በዚህም ቴፒ ከተማ በታሪኳ አስደሳች ስኬት አስመዝግባለችም ብለዋል።

የቴፒ ከተማ ከንቲባ አቶ ገላቲያስ ሻሜ እንደገለፁት  ፣ይህ ስኬት እንድመዘገብ የራሳቸውን አሻራ ላሳረፉ አካላት ምስጋና አቅርበው የከተማውን ህዝብ በማስተባበር ክለቡን የማጠናከር ሥራ ይሠራልም ብለዋል።

የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የውኃ፣ ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የዞኑ የስፖርት ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላቸው ጋራ ፣ስፖርት ትልቅ የልማት መሳሪያ መሆኑን ተናግረው በዞኑ የአንድነትና የፍቅር ተምሳሌት መሆን መቻሉን አስመስክሯል ብለዋል።

በወቅቱ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎችን ማመቻቸት ከሁሉም የሚጠቅ መሆኑን የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዓለማየሁ ዓለሙ የተናገሩ የሲሆን በዚህም አካባቢያቸውን የሚያስተዋውቁ ሌሎች ስፖርተኞችን ማፍራት ይጠበቃልም ይጠበቃልመ ብለዋል።

የቴፒ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ቴፒ ሲደርስ ከበቆ ቀበሌ ጀምሮ የቴፒ ከተማ እና የየኪ ወረዳ ነዋሪዎች አቀባበል በማድረግ የተለያዩ ማበረታቻ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።