የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት ጳጉሜ 3 “የፅናት ቀን” በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
የ2018 የጳጉሜ ቀናት የኢትዮጵያን የትግል፣ የፅናትና የተስፋ ታሪክ በማስታወስ፣ የተሻለ ነገን ለመገንባትና የጋራ ሀገራዊ ኃላፊነትን ለማጠናከር በተለያዩ ስያሜዎችና ዝግጅቶች በመላው ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ይገኛሉ።
በእነዚህ ቀናት ዜጎች በጋራ በመቆም ለሀገር እድገት፣ ለህዝቦች አብሮነትና ለዘላቂ ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያድሱበትና የተስፋን ብርሃን የሚሰንቁበት አጋጣሚ ነው።
ቀኑ ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ሌት ተቀን በጽናት ለሚቆሙት ብርቱ የፀጥታ ኃይሉ ቅድሚያ የሚሰጥበት፣ እንዲሁም ለሀገረ-መንግሥት ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉ ጀግኖች ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የሚታወስበት ነው።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት በመገንባት በራስ የመቆም አቅሟን ያረጋገጠችበት ወቅት በመሆኑ፣ ይህንኑ ስኬት ለሕዝቦቿ ሰላምና ለሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገት መሠረት በማድረግ ሀገራዊ ጽናትን በተጨባጭ ልማት ለማጽናት ቃል ኪዳን የተታደሰበት ልዩ ቀን።
በዚህ ታሪካዊ ቀን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምረው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች በአደባባይ በመሰብሰብ የሀገራችንን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና የተመዘገቡ ታላላቅ ድሎችን የሚዘክሩ ልዩ ልዩ መልዕክቶችን በማንገብ ቀኑን እያከበሩ ይገኛል። የክልሉ መ/ኮ እንደዘገበው።
More Stories
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በኢንተርፕራይዝ ልማት በኩል 2መቶ95 ቢሊየን ብር የገበያ ትስስር መፈጠሩን ገለፀ
ዘላቂ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ፣ አካታች የፖለቲካ ባህል እና የሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ መደላድል