ጣሊያናዊው የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ በ66 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ፍራንኮ ባሬዚ የጣሊያን ብሔራዊ ቡድንን ከፈረንጆቹ 1982 እስከ 1994 ያገለገለ ሲሆን ለሀገሩ 81 ጨዋታዎችን አድርጓል፡፡
ባሬዚ በፈረንጆቹ 1982 ከጣሊያን ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫን አሳክቷል፡፡
20 ዓመታትን በኤሲሚላን ቤት በተጫዋችነት ያሳለፈው ፍራንኮ ባሬሲ ለ15 ዓመታት ቡድኑን በአምበልነት መምራቱ ይታወሳል፡፡
በኤሲሚላን ቆይታው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እና የጣሊያን ሴሪ አን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡
ፍራንኮ ባሬዚ ለጣሊያኑ ክለብ ኤሲሚላን በሁሉም ውድድሮች 719 ጨዋታዎችን አድርጎ 33 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል