አሰልጣኙ ከወራት በፊት ባርሴሎናን እለቃለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም ውሳኔውን እንደቀየረ አሳውቆ ነበር
ባርሴሎና ጀርማናዊውን ሀንሲ ፍሊክ የዣቪ ተተኪ ለማድረግ ማሰቡ ተገልጾ ነበር
ባርሴሎና አሰልጣኙ ዣቪን አሰናበተ፡፡
የስፔኑ ባርሴሎና እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ዣቪ ሄርዳንዴስን አሰናብቷል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ዣቪ ከወራት በፊት ባርሴሎናን ከዘንድሮው ውድድር መጠናቀቅ በኋላ ክለቡን እንደሚለቅ አሳውቆ ነበር፡፡
ይሁንና ባርሴሎና ከአሰልጣኙ ጋር ባደረጋቸው ውይይቶች ዣቪ በአሰልጣኝነቱ እንዲቀጥል መስማማቱንም አሳውቆ ነበር፡፡
ባርሴሎና ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሰልጣኝ ዣቪ ከአሰልጣኝነት ማሰናበቱን ገልጿል፡፡
የ44 ዓመቱ ዣቪ ላለፉት ሶስት ዓመታት የልጅነት ክለቡን ሲያሰለጥን ቆይቷል፡፡
ባርሴሎና ጀርመናዊውን ሀንሲ ፍሊክ የዣቪ ተተኪ ለማድረግ ውይይቶች በመደረግ ላይ እንደሆኑ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አሰልጣኝ ዣቪ በባርሴሎና ቆይታው አንድ የስፔን ላሊጋ ዋንጫ እና ሱፐር ካፕ ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል፡፡
Al-Ain
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል