August 18, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሸካ ዞን የማሻ ከተማ ከንቲባ አንዱዓለም ጌታቸው ለከተማው ምክር ቤት የ2018 የአስፈጻሚ አካላት የስራ ሪፖርት አቀረቡ።

የማሻ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማሻ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

‎በዚህም በበጀት ዓመቱ ‎በኢኮኖሚ ዘርፍ ለ946 የዜጎች ስራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን በከተማ ግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ስራ መስኮች ተጠቃሚ መሆናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዋል።

‎‎ከመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ትብብር ከ41 ሚለየን ብር በላይ ለተለያዩ ስራ መስኮች ብድር ተሰራጭቷል።

‎‎ቀጥተኛ ካልሆነ የተሰበሰበ ታክስ 85 በመቶ በላይ መሆኑና ከታክስ ኦዲት የተገኘ ገቢና ህገ ውጥ ነጋዴዎችን ህጋዊ የማድረግ ስራ በጉባኤው በጠንካራ ጎን ተነስቷል።

‎‎በቀጣይ በርብርብና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተብለው በምክር ቤቱ አባላት ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ገቢን አሟጦ አለመሰብሰብ ፤ ኮንትሮባንድና የነዳጅ ቁጥጥር መላላት፣ጊዜ ያለፈባቸው ምግብና ምግብ ነክ ቁጥጥር ሥራ ማነስ ፣ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች አለመቀላጠፍ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት ቁጥጥር ማነስና ሌሎችም በመድረኩ በስፋት ቀርበዋል።

‎‎ ጎሬ – ማሻ-ቴፒ አስፓልት ስራ ካሳ ክፍያ ግልጸኝነት ጉድለት፣ የመሬት አቅርቦት፣ በማሻ ከተማ የተጀመረው የንጹሕ መጠጥ ውሃ ግንባታ መዘገየትና የባለድርሻ አካላት ትኩረት ማነስ፣ የመብራት ተደራሽነት እንዲሁም ለህዝባዊ አገልግሎት የተገነቡት ኘሮጀክቶች በወቅቱ ተጠናቀው ለአገልግሎት ያለመብቃቸውን ከምክር ቤቱ አባላት በኢኮኖማ ዘርፍ የተነሱ ዐቢይ ጉዳዮች ሲሆኑ ጉባኤው በ2ኛ ቀን ውሎው ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።