ምክር ቤቱ እያካሄደ የሚገኘው ይህ 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባዔው ሲሆን፣ በሁለት ቀን ቆይታውም የተጠናቀቀውን 2018 በጀት ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ጉባዔው ለክልሉ ህዝብ ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደር መረጋገጥ የሚረዱ ልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆችን፣ እና ደንቦችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይገመታል።
በጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች እና የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል።
More Stories
የባህር በር – የኢትዮጵያ የፍትህና የልማት ጥያቄ
የኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጥሪ
በምክክሩ ለሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በነጻነት ተወያይተናል – ተመካካሪዎች