የአፍሪካ እና የባሕረ ሰላጤው (ገልፍ) ሀገራትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል የተባለው “የባሕረ ሰላጤው (ገልፍ) እና አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር መድረክ” በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
መድረኩ በአፍሪካ እየጨመረ የመጣውን የባሕረ ሰላጤው (ገልፍ) ሀገራት የኢንቨስትመንት ፍሰት በመጠቀም የኢንዱስትሪ መስፋፋትን፣ የኢኮኖሚ ሽግግርን እና ዘላቂ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን እንዴት ማፋጠን እንደሚቻል ለመምከር ያለመ ነው።
በአሁኑ ወቅት የባሕረ ሰላጤው (ገልፍ) ቀጣና ለብዙ የአፍሪካ ሀገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ አስፈላጊ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ አጋር እየሆነ መጥቷል።
በመሆኑም የሀገራቱ ኢንቨስትመንት ከባህላዊ ዘርፎች አልፎ በዘመናዊ የልማት መስኮች ላይ በማተኮር በመሠረተ ልማት እና ሎጂስቲክስ፣ በታዳሽ ኃይል እና ግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ እና የፋይናንስ አገልግሎቶች እንዲሁም የዲጂታል ፈጠራዎች ን ያካተቱ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በመተግበር ላይ ትገኛለች። ይህም ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት፣ ቀጣናዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ ገበያዎች ተወዳዳሪ በር ለመሆን ያለመ ነው ተብሏል ።
ከየባሕረ ሰላጤው (ገልፍ) ሀገራት ጋር የቆየና የጠበቀ ግንኙነት ያላት ኢትዮጵያ፣ ይህ መድረክ ነባሩን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ እና አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመሳብ ወሳኝ አጋጣሚ እንደሚፈጥርላት ተገልጿል።
NBCEthiopia
More Stories
አሜሪካ በኢራን ጦርነት ከ37 ቢሊየን ዶላር በላይ እንዳወጣች ተገለፀ::
ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ማኅበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚያግደው ሕግ በፈረንሳይ ምክር ቤት ጸደቀ።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የባዮጋዝ የምርምር ማዕከል ለአፈር ለምነትና ለግብርና ምርታማነት አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው