August 12, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፒኤስጂ የትኛውም ክለብ ያልስራውን ታሪክ መስራት ይችል ይሆን?

የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ለተከታታይ ሁለት አመታት በማሳካት በታሪክ ሁለተኛው ክለብ መሆን የቻለው የፈርንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ በሚቀጥለው የውድድር አመት በስደስት የተለያዩ ውድድሮች ላይ የሚሳተፍ መሆኑን ተከትሎ ምን አልባት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ጨምሮ የሚሳተፍባቸውን ስድስቱንም ዋንጫዎች ማሳካት የሚችል ከሆን በታሪክ የመጀመሪያው ክለብ መሆን ይችላል።

ዛሬ በአውሮፓ ሱፕር ካፕ ዋንጫ ከአስቶን ቪላ ጋር በሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ አንድ ብለው የሚጀምሩት ፒኤስጂዎች ባሳለፍነው የውድድር አመት በጎረቤታቸው ፓሪስ እግር ኳስ ክለብ ከተነጠቁት የፈረንሳይ ዋንጫ ውጪ ​የዩኤፋ ሱፐር ካፕ፣ የፈረንሳይ ሱፐር ካፕ፣ የፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ፣ ሊግ አንድ እንዲሁም ​የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ አምስት የተለያዩ ውድድሮችን ማሳካታቸው ይታወሳል።

በዘንድሮው የውድድር አመት የጎደለችውን ዋንጫ በመሙላት የሚያጠናቀቁ ከሆን በታሪክ የመጀመሪያው ከለብ መሆን ይችላሉ።

በቅርቡ በተጠናቀቀው ዓለም ዋንጫ ላይ 16 ተጫዋቾችን ውደ ሰሜን አሜሪካ የላከው ፒኤስጂ ከስፔን ጋር ዋንጫውን ካሳካው ፋቢያን ሩይዝ ጨምሮ ስድስት ተጨዋቾች እስከ ፍፃሜው ሳምንት ድረስ መጫዎት ችለዋል።

እነዚህ ተጨዋቾች በቀጣይ እሮብ ከአስቶንቪላ ጋር እስከ ሚያደርጉት ሱፐር ካፕ የፍጻሜ ጨዋታ ድረስ ያላቸው የእረፍት ጊዜ 24 ቀናት ብቻ መሆኑ ምን አልባት የሉዊዝ ኤነሪኬውን ስብስብ ሊጎዳው ይችላል