ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3 ሺ ሜትር መሰናክል ፍጻሜ አልማዝ ዮሀንስ እና ወሰኔ አሰፋ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያውን ወስደዋል።
በአሜሪካ እየተደረገ በሚገኘው ውድድር አልማዝ ዮሀንስ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች። 9 ደቂቃ 15.81 ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ሰዓት ሲሆን በዓመቱ ውስጥ ከተመዘገቡት ፈጣን ሰዓቶችም አንዱ ነው።
2ኛ ደረጃን ይዛ የጨረሰችው አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9 ደቂቃ 30.50 በመግባት የዓመቱን ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ የብር ሜዳሊያውን ለሀገሯ አስገኝታለች።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል