በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ በአንድነት ቀበሌ በ190ሚሊዮን ብር በላይ በጀት የሚገነባው አዲሱ ዘመናዊ የሕዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል ።
የእንካን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሸካ ዞን ምክትል አስተዳደርና የውሃ፣ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ በላቸው ጋራ በወቅቱ እንደተናገሩት የመናኸሪያ ግንባታው የህብረተሰቡን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስና ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ወሳኝ በመሆኑ ለዚህም የክልሉ መንግስት ለሰጠው ምላሽ አመስግነዋል ።
የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፓርት ቢሮ ኃላፊ ፋጂኦ ሳፒ አዲሱ መናኸሪያ የቴፒ ከተማን የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያሳድግ ከመሆኑም በላይ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ የቆየውን የትራንስፖርት መናኸሪያ እጥረትና መጨናነቅ በዘላቂነት ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል ።
መናኸሪያያው 400 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችልና ግንባታውም በአንድ አመት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል ።
ግንባታው በተቀመጠለት የጥራት ደረጃና የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ የክልሉ መንግሥት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ