ዞን አቀፍ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ የዕቅድ አፈፃፀም ማጠቃለያና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የሸካ ዞን ሰላም፣ ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዋስሁን አውሎ እንደገለፁት ወሳኝ ኩነት በመንግስት ትኩረት ሰጥቶት የሚሰራ መሆኑን ገልፀው እስከ ቀበሌ መዋቅር ድርስ በተቀናጀ መልኩ ሊተገበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በዲጂታል ሲስተም በመታገዝ ምዝገባ መፈፀም፣ሪፖርት በወቅቱ ማቅረብ፣ባለሙያዎች በስነ-ምግባርና በቅንጅት ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል።
በቀጣይ እያንዳንዱ ኩነቶች ሙሉ በሙሉ በሚመዘገቡበት ሂደት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዘላቂነት እንዲሠሩ አሳስበዋል።
በዞኑ የወሳኝ ኩነት ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ጋሪፎ የወያያ ሰነድ ቀርቦ በአፈፃፀሙና ለቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በአምስቱም መዋቅሮች የተሻለ አፈፃፀም ያለመኖሩን ገልፀው ለዚህ ተግዳሮት የሆነው ሪፖርት በወቅቱ ያለማቅረብ፣ዲጂታል ምዝገባ በተግባር ያለመፈፀም ክፍተቶች ለአፈፃፀሙ ተግዳሮት መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል በወሳኝ ኩነት ምዝገባና ብሔራዊ መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 760/2004 እና በአዲሱ የሲቪል እና ቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 1370 ተሻሽሎ የቀረበ አንቀጽም ይፋ ተደርጓል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሪፖርቱ ለቀጣይ ስራቸው የሚያነቃቃና የተሻለ መሆኑን ገልፀው የሲስተም ችግር፣በወቅቱ ዕቅድ ያለማዘጋጀት፣የእድሜ ማጭበርበር ችግሮች መኖራቸውን ገልፀው ለቀጣይ ይህን በመቅረፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባም ተናግረዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።
እንደሀገር ”በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሸካ ዞን በማሻ ማረሚያ ተቋም ተካሂዷል።