ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ያስቆጠረው ማዕከሉ ከ1ሺህ 286 በላይ ለሆኑ ዜጎች አገልግሎት ተደራሽ ማድረጉም ተገልጿል።
ቀደም ሲል የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት ከቢሮ ቢሮ መመላለስና ረዥም ጊዜ መቆየት የተለመደ መሆኑን የገለፁት ተገልጋዮቹ አሁን ላይ በቴፒ ከተማ አገልግሎት እየሰጠ ያለ መሶብ የአንድ ማዕከል ይህንን ታሪክ እየቀየረ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ያለ ምንም እንግልት በአንድ ማዕከል የተለያየ አገልግሎት እያገኙ መሆኑን የገለጹት ተገልጋዮቹ አሰራሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ሀሳብ ሰጥተዋል።
የቴፒ መሶብ አንድ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር መለሰ ናኑ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ተመርቆ ሥራ የጀመረው ይህ ዘመናዊ ማዕከል፣ የተለያዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ስር በማጠቃለል የሕዝቡን ድካም በማቅለል አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ማዕከሉ ከተበታተነ አሰራር ወጥቶ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ከማሰባሰቡም በላይ በቴክኖሎጂ የታገዘ የኦንላይን አገልግሎት በመስጠት ወደ ዲጂታል ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ያሸጋገረ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም እስካሁን ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ ከ1 ሺህ 286 በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፣ ሕዝቡ ይህንን ዕድል ተጠቅሞ ያለምንም ስጋት አገልግሎት እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።