የ2018 ዓ.ም የሸካ ዞን አዳሪ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት የወላጆች በዓል በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ተካሂዷል።
በመረሀግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን አለሙ ተቋሙ ከተመሰረተ ሁለት ዓመት ማስቆጠሩን አስታውሰው 119 ተማሪዎችን በመቀበል ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
አዳሪ ት/ቤት መመስረቱ በዞኑ የተሻለ የትምህርት ጥራት እያዲመዘገብ ትልቅ እድል የፈጠረ መሆኑን ተናግረው በሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ለዞኑ ተስፋ ሰጪ ተማሪዎችን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህም የሸካ ልማት ማህበር፣የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲና የበርካቶች የልፋት ውጤት መሆኑንም ጠቁመዋል።
አክለውም ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ የማጣቀሻ መጽሐፍትና የድጋፍ ሰራተኞችን በመመደብ በርካታ ተግባራት እየተከናኑ መሆኑን ገልፀው ይህን ለማጠናከር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም ጠይቀዋል።
በወቅቱ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ዘላለም ከበደ እንደገለፁት የውስጥ ሱፐር ቪዥን መደረጉ፣በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የማጠናከሪያ ትምህር መሰጠቱ፣ለተማሪዎች ስፖርታዊ ውድድር በማዘጋጀት ተማሪዎች እንዲሳተፋ ማድረግ ከመቻሉ በተጨማሪ አንድ ተማሪ ወደ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ት/ቤት እንዲዘዋወር የተደረገና ሌሎች በርካታ አስተዳደራዊ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የዞኑ ልማት ማህበር እያደረገ ያለው ጥረት የሚደገፍ መሆኑን ተናግረው በዚህም ለውጦችን ለማምጣት የተማሪ ማረፊያ ማሻሻል፣የሎጂስቲክስ ችግሮችን ለመቅረፍ ሊሰራበት እንደሚገባም አንስተዋል።
በስፍራው የተገኙት የተማሪ ወላጆች እንደገለፁት ተማሪ፣ወላጅና መምህር በጋራ በመቀናጀት የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግብ እንደሚችል ጠቅሰው የምስተዋሉ ችግሮችን በመወያየት መፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ቀጣይነት ያለው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲጠናከርም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ክትትልና ድጋፍ ልጠናከር እንደሚገባም ተናግረዋል።
የ2018 ዓ.ም አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት እንዲሁም የ2019 ዓ.ም እቅድ ላይ ሀሳብና አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን በሚመለከተው አካል ምላሽና ማብራርያ መድረኩ ተጠናቋል።
More Stories
መሣሪያን በብዕር የተኩ እጆች፤ የሀገራዊ ምክክር ታሪካዊ ምዕራፍ
የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተሰነዘረውን የጥቃት ሙከራ ተከትሎ ዋሽንግተን ኢራን ላይ “ከፍተኛ” ጥቃት ፈጸመች
ከማሻ ደገሌ መንገድ በእጅጉ በመበላሸቱ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ችግር እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ቅሬታ አቀረቡ