የአሜሪካ ጦር ኢራን በዋሽንግተን ኃይሎች ላይ ለሰነዘረቻቸው የሚሳዔል ጥቃት ሙከራዎች የአጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት ሲል፤ ረቡዕ ምሽት ኢራን ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈፀሙን አስታውቋል።
በዚህ ጥቃት “በርካታ” የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዒላማዎች መመታታቸውን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ገልጿል።
ተቀዛቅዞ የነበረው ጥቃት በድጋሚ የተጀመረው፤ ማክሰኞ ዕለት ኢራን በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች እንዲሁም በሆርሙዝ ወሽመጥ ጉዞ ላይ በነበሩ መርከቦች ላይ ሚሳዔሎችን በማስወንጨፏ እንደሆነ ዕዙ ተናግሯል።
በአሜሪካ ጥቃት የኢራን “ወታደራዊ የዕዝ ማዕከላት፣ የሜሳዔል እና የድሮን ተቋማት፣ የባሕር ዳርቻ ቁጥጥር እና መከላከያ ስፍራዎች፣ እና የባሕር ኃይል አቅሞች” ዒላማ መደረጋቸውም ተገልጿል።
አሜሪካ ለ13 ተከታታይ ቀናት ጥቃት ስትፈጽምበት፤ ኢራንም አጸፋውን ስትመልስበት የቆየው ግጭት ለቀናት አንጻራዊ መረጋጋት ከታየበት በኋላ በድጋሚ ተቀጣጥሏል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ “እጅግ ወዳጅነት የተሞላባቸው ድርድሮች” እየተካሄዱ መሆኑን ተናግረው የነበር ቢሆንም ኢራን በበኩሏንግግር ተጀምሯል መባሉን አስተባብላለች።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ