ለዘመናት አገልግሎት እየሰጠ የነበረውና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሸካ ዞንን ከኢሉባቦር ዞን ወረዳዎች የሚያገናኘው ከማሻ ደገሌ መንገድ በእጅጉ በመበላሸቱ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ችግር እንደፈጠረባቸው ነዋሪዎች ቅሬታ አቀረቡ ።
ጣቢያችን ያነጋገረው የማሻ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ቅሬታውን ታሳቢ ያደረገ ምላሽ ለመስጠት እየሰራሁ ነው ብሏል።
=============================
መንገድ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው በላፈ ህዝብ ለህዝብ ግንኙት አይነተኛ ሚና ያለው ቢሆንም በጋ ከክረምት ያስጠቅማቸው የነበረው ከማሻ-ደገሌ መንገድ በመበላሸቱ መቸገራቸው ነው ወጣት ባየሁት አየለና ኤፍሬም ዓለሙ የሚናገሩት፦
ህብረተሰቡ ጠያቂ ብቻ ሳይሆን የልማቱ ተሳታፊ በመሆን ለጥገና ሀብት አሰባስቦ የነበረ መሆኑን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ
አሰሪው አካል ወቅቱን ያልጠበቀና ከደረጃ በታች ጥገና በመደረጉ ችግሩ መባባሱን ይናገራሉ።
ከማሻ ደገሌ መንገድ ከተሰራ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ከቅርብ አመታት ወዲህ ብልሽቱ ከፍተኛ በመሆኑ በህዝቡ ላይ እያደረሰ ያለው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራን ለመታደግ ሀብት የተሰበሰበ ቢሆንም የታለመው እንዳልተሳካ በቀበሌው የህብረተሰብ ተሳትፎ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል አቶ ሻርፎ ጋወቶ ያስታውሳሉ፦
አሁንም ቢሆን ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ አበርክቶ እንደሚኖር ያመላከቱት አቶ ሻርፎ ከወረዳው መንግስት በኩል ወቅታዊነትና ጥራት ላይ ያተኮረ ስራ እንደሚጠበቅም አውስተዋል፦
ባለፈው በጀት ዓመት በ22 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ በወጣው ጨረታ መሰረት ከኮንትራክተሩ ጋር ውል ተፈጽሞ ወደስራ መገባቱን የሚያስታውሱት የማሻ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ
ሳሙኤል ገሪቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መናርና ወቅቱ ክረምት መሆኑ ተግዳሮት እንደፈጠረ አብራርተዋል።
በ 2019 የበጀት ዘመን ቅሬታውን ታሳቢ ያደረገ መፍትሔ ለማበጀት ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ እየተሰራ መሆኑን ያወሱት ኃላፊው መንገዱ ተጠግኖ ለትራፊክ ክፍትሲሆን አጎራባች ወረዳዎችን ጭምር ያገናኛል ብለዋል።
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የሥራ ዘመኑን የማጠቃለያ ጉባኤ በታርጫ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሳይበር ጥቃት ሰነዘረ!