በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለሀገራችን የወደፊት ዕጣፈንታ ወሳኝ በሆኑ የሀገር ግንባታና የሰላም ጉዳዮች ላይ በነጻነት ተወያይተናል አሉ የምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች፡፡
በኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ተመካካሪዎች የምክክር ሂደቱ ልዩነቶችን ለማጥበብና የጋራ ትርክት ለመፍጠር መሰረት መጣሉን አንስተዋል፡፡
ሀገራችን በእርስ በርስ ግጭቶችና በመጠላላት ብዙ ዋጋ የከፈለችባቸው ጊዜያት ሊያበቁ ይገባል ያሉት ተመካካሪዎቹ፤ ልዩነትን የሚያጎሉ ትርክቶችን ወደ ጎን በመተው በጋራ የምናድግባት ሀገር ለመገንባት ምክክሩ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህም መጪውን ትውልድ ማዕከል ያደረገና ሀገርን በዘላቂነት ሊያሻግሩ በሚችሉ ሀሳቦች ላይ በስፋት መምከራቸውን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በሚወስኑ፣ ሰላምና ዴሞክራሲን በሚያሰፍኑ ወሳኝ የሀገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ በነጻነት መወያየታቸውን ጠቁመዋል።
ዜጎች በአንድ ላይ ቁጭ ብለው በመነጋገር ችግሮችን መፍታት መቻላቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ሀገሩን እንዴት ማስቀጠል እንዳለበት ጠንካራ መሠረት የጣለ ነው ብለዋል፡፡
More Stories
የባህር በር – የኢትዮጵያ የፍትህና የልማት ጥያቄ
የኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጥሪ
ኢትዮጵያ የደን ሽፋንን በማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋም የምታከናውነውን ጥረት ኖርዌይ ትደግፋለች