አሜሪካ በኢራን ጦርነት ወደ 37 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገንዘብ ማውጣቷን የመከላከያ ሚኒስትሩ ፔት ሄግስት ገልጸዋል።
ይህም ባለፈው ግንቦር ወር ላይ ይሆናል ከተባለው ገንዘብ አንጻር የ8 ቢሊየን ዶላር ጭማሪ እንዳለው ቢቢሲ አስነብቧል።
ሚኒስትሩ ለሴኔቱ በሰጡት ማብሪሪያ ለመከላከያ መስሪያ ቤቱ ተጨማሪ 87 ቢሊየን ዶላር እንዲመደብ ጠይቀዋል።
ከዚህ ውስጥ 67 ቢሊየን ዶላሩ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚካሄድ ዘመቻ የሚውል መሆኑን ዘገባው አስታውሷል።
ባለፈው ሚያዝያ ወር ለቀጣዩ ዓመት የመከላከያ በጀት 1 ነጥብ 5 ትሪሊየን ዶላር እንዲመደብ ኋይት ሐውስ መጠየቁን ዘገባው አስታውሷል።
አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ግጭት ከገቡ 11ኛው ቀናቸውን የያዙ ሲሆን፥ አሜሪካ በቴህራን መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ስትፈጽም ኢራን በበኩሏ በቀጠናው አገራት በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ መገልገያዎችና መሰረተ ልማቶች ላይ አፀፋዊ እርምጃ ወስዳለች።
BBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ