ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው የባዮጋዝ የምርምር ማዕከል ለአፈር ለምነትና ለግብርና ምርታማነት እድገት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስታወቀ።
ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን የግብርና ስራን ለማዘመንና ለማስፋፋት የድርሻውን እየተወጣ መሆኑ ተመላክቷል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤፍሬም ዋቅጅራ ለኢዜአ እንደገለጹት በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የተገነባው የባዮ ጋዝ የምርምር ማዕከል ሀይልን ከማመንጨት በተጨማሪ የስልጠና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ይጣል የነበረውን ተረፈ ምርት በመሰብሰብ ባዮ ጋዝ በማምረት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ማዕከሉ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት የአፈር ለምነት ለመጠበቅና ለግብርና ምርታማነት እድገት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ነው ያሉት።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ዲን ሰለሞን ቱሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የግብርና ስራዎችን ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
#ኢዜአ
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ