2018 በጀት ዓመት የተቋማት ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ በማሻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
አቶ በላቸው ጋራ የሸካ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በመድረኩ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር እንደገለፁት በዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች በባለፈው በጀት ዓመት ታቅደው በተከናወኑ ተግባራት መሠረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች እየተመለሱ መምጣቱን ገልፀው ከሚጠበቀው አንፃር ግን ብዙ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
አቶ በላቸው አያይዘውም በግብርና፣ንግድ እና ገበያ ልማት፣ከተማ ልማት፣እና በገቢ አሰባሰብ ተቋማት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ወቅታዊ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር፣የኮሪደር ልማት ስራን ማፍጠን እና የግብር አሰባሰብ ስርዓቱን ማዘመን እንዲሁም ተቋማት የአፈፃፀማቸውን ደካማና ጠንካራ ጎን በመለየት ቀጣይ የተሻለ ለመስራት መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የሸካ ዞን ፕላን እና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጸያጻ በለጠ የ2018 በጀት ዓመት የተቋማት ማጠቃለያ ሪፖርት ለተሳታፊዎች እንቀረቡ ይገኛል።
#ዞን መንግስት ኮምኒኬሽን
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ