በ2010 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ዓመታዊ የወጪ ንግድ ገቢ 2.66 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንደነበረ ያወሳው የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዘርፉን ለማሳደግ ባለፉት ዓመታት በተደረገ የሪፎርም እርምጃዎች በታሪክ ከፍተኛ የተባለውን የወጪ ንግድ ገቢ ለማስመዝገብ ተችሏል ሲል አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 7.25 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ እንደነበረ የጠቀሰው ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ፣ የበጀት ዓመቱ ሊጠናቀቅ የሁለት ወራት ጊዜ በቀረበት በዚህ ወቅት በ10 ወራት ውስጥ ብቻ ወደ 8.71 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመገኘቱ የዕቅዱን 120.17 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ገልጿል።
ይህ ዕድገት ሊመዘገብ የተቻለባቸው ምክንያቶች አንዱ የወጪ ንግድ ምርቶችን ዓይነት ማብዛት በመቻሉ እና በጥራት ረገድ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ለማሳደግ በመሠራቱ እንደኾነ ያመላከተው የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር የወጪ ንግድ ምርቶች ጥራትን ለማስጠበቅ በተሠራው ሥራ ጥራታቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪነታቸው የላቀ ምርቶችን ማቅረብ በመቻሉ የኢትዮጵያን ምርቶች የሚቀበሉ አዳዲስ የውጭ ሀገራት የገበያ መዳረሻዎችን ቁጥር መጨመሩ ለገቢው ማደግ ዋና ምክንያት ነው ብሏል
ሚንስቴር መሥሪያ ቤቱ ስኬቱ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሬ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍና የኢኮኖሚውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ትልቅ ተስፋ የሰጠ እንደኾነ በወል ትስስር ገጹ ማስፈሩን ትርታ ተመልክቷል።
ዓመታዊ የወጪ ንግድ ያስገኘው ገቢ ጨምሯል ተባለ
More Stories
የነገ ትውልድ ተስፋ አረንጓዴ ልማትና ቱሪዝም
ህገ ወጥ የቡና ግብይት ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚገባ የካፋ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ ።
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው