ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ያገኘችውን የማዕድን ሀብት በጥሬው ወደ ውጭ ከመላክ ባለፈ፣ እሴት ጨምሮ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት በማዋል ረገድ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች።
ከሪፎርሙ በፊት ዘርፉ ለሀገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከአንድ በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ማዕድንን የኢኮኖሚው ዋነኛ ምሰሶ በማድረግ የኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት እንዲሆን ተደርጓል።
ይህም በየዓመቱ ለነዳጅ፣ ለማዳበሪያና ለብረት ግብዓቶች ግዢ የሚወጣውን ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው።
በተለይም በብረት ማዕድን ዘርፍ ከ1.1 ቢሊዮን ቶን በላይ ክምችት ላይ በመመስረት በዓመት ሦስት ሚሊዮን ቶን ብረት በሀገር ውስጥ ለማምረት ሰፊ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
በወርቅ ምርት ዘርፍም ቢሆን ከ2010 እስከ 2017 ባሉት ዓመታት ውስጥ የ1241.4 በመቶ ከፍተኛ የኤክስፖርት ዕድገት መመዝገቡ የሪፎርሙን ውጤታማነት በተጨባጭ ያሳያል። በተጨማሪም በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ አማካኝነት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 4.85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል።
More Stories
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ የአቮካዶ ምርቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እያደረጓት ነው
ከወጪ ንግድ 607 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
በጅማ ዞን የተመረተ ከ6.7 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የአቮካዶ እና የሙዝ ምርት ለገበያ ቀረበ