አርሰናል የዘንድሮውን የውድድር ዘመን በታላቅ ታሪክ ለማጠናቀቅ በዝግጅት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ ለደጋፊዎቹ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መረጃ ወጥቷል።
እንደ ዴይሊ ሜይል እና ያሁ ስፖርት ዘገባ፣ መድፈኞቹ የፕሪሚየር ሊግ እና የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን በአንድ ላይ የሚያከብሩበትን የድል ሰልፍ (Trophy Parade) እቅድ ይፋ አድርገዋል።
በወጣው መርሃ ግብር መሰረት፣ አርሰናል አንዱን ወይም ሁለቱንም ታላላቅ ዋንጫዎች ካሸነፈ የድል ሰልፉን እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በሰሜን ለንደን ኢስሊንግተን ጎዳናዎች ላይ ያካሂዳል።
ሰልፉ የሚጀምረው ቡድኑ በቡዳፔስት ከፒኤስጂ ጋር ከሚያደርገው የሻምፒዮንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ማግስት፣ ጠዋት ወይም በምሳ ሰዓት እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።
ይህ እቅድ በሀንጋሪ የሚካሄደውን የፍጻሜ ጨዋታ ለመታደም ለሚጓዙ ደጋፊዎች ትልቅ የቤት ስራ ሆኖባቸዋል።
ጨዋታው ቅዳሜ ምሽት ተጠናቆ እሁድ ጠዋት ለንደን በሚካሄደው የክብር ሰልፍ ላይ ለመታደም ደጋፊዎችና ተጫዋቾች ጫና ውስጥ መግባታቸው ስጋት ፈጥሯል።
አርሰናል በአሁኑ ወቅት በሊጉ ሰንጠረዥ ማንችስተር ሲቲን በ5 ነጥብ ልዩነት እየመራ ይገኛል። መድፈኞቹ ቀሪዎቻቸውን የዌስትሃም፣ በርንሌይ እና ክሪስታል ፓላስ ጨዋታዎች በአሸናፊነት ካጠናቀቁ፣ ከ22 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ያነሳሉ።
በሻምፒዮንስ ሊጉም ከሃያ ዓመታት በኋላ ለፍጻሜ ደርሰው ከፒኤስጂ ጋር ይጫወታሉ።
በመሆኑም የሰሜን ለንደኑ ክለብ ደጋፊዎች ግንቦት 23ን በታላቅ ጉጉት እየጠበቁ መሆኑን ዴይሊ ሜይል እና ያሁ ስፖርት ዘግበዋል።
More Stories
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የእግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ተባለ
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ