የእግር ኳስ ጸሐፊዎች ማህበር (FWA) የ2025/26 የውድድር ዘመን የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ምርጫውን ይፋ ሲያደርግ የማንችስተር ዩናይትዱን አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝን አሸናፊ አድርጎ መርጦታል።
እንግሊዝ የሚገኙ ከ900 በላይ የማህበሩ አባላት በሰጡት ድምፅ መሰረት፣ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ሊያሸንፍ ችሏል።
ይህ ስኬት ለአማካዩ ጥሩ የታሪክ አጋጣሚ ሲሆን፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ2010 ዋይን ሩኒ ካሸነፈ በኋላ ሽልማቱን ማሸነፍ የቻለ የመጀመሪያው የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሆኗል።
ፈርናንዴዝ በዚህ የውድድር ዘመን ለቀያይ ሰይጣኖቹ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 34 ጨዋታዎች 8 ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፍ 20 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝን በመከተል ፣ ዴክላን ራይስ እና ኤርሊንግ ሀላንድ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
More Stories
የአርሰናል የድል ሰልፍ በለንደን ጎዳናዎች፤ ለታሪካዊው ቀን ቀጠሮ ተይዟል!
አርሰናል ከ20 ዓመት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ ደረሰ
ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን በማሸነፍ የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን አረጋገጠ