በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡
11 ሰዓት 30 ላይ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የማንቼስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ማቲያስ ኩኛ፣ ቤንያሚን ሼሽኮ እና ኮቢ ማይኖ አስቆጥረዋል፡፡
ሊቨርፑልን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦችን ደግሞ ዶሚኒክ ሶቦዝላይ እና ኮዲ ጋክፖ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ዩናይትድ በቀጣይ የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆኑን አረጋግጧል፡፡
አስቀድሞ በተደረገ በሌላ የሊጉ መርሐ ግብር ቦርንማውዝ ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል አስቶንቪላ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በሜዳው ቪላ ፓርክ ቶተንሃም ሆትስፐርን ያስተናግዳል፡
More Stories
ኢትዮጵያዊ በዳምጠው ከበደ ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ