ባለፈው እሁድ በተካሄደው የለንደን ማራቶን አትሌት ሰባስቲያን ሳዌ 1 ሰዓት ከ59 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ በመግባት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን ተከትሎ፣ በኬንያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ አትሌቱን በቤተ መንግሥት ተቀብለው ላስመዘገበው ድንቅ ውጤት በአጠቃላይ የ8 ሚሊዮን የኬንያ ሽልንግ የገንዘብ ሽልማት አበርክተውለታል። ይህ ታሪካዊ ስኬት በዓለም አትሌቲክስ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻም በተመሳሳይ ከሁለት ሰዓት በታች በመግባት ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል።
ከገንዘብ ሽልማቱ በተጨማሪ ፕሬዝዳንት ሩቶ ለአትሌቱ ልዩ የክብር ስጦታ አዘጋጅተዋል። ሳዌ የፈለገውን መኪና እንዲመርጥ የተፈቀደለት ሲሆን፣ የመኪናው ታርጋም ታሪክ በሠራበት ሰዓት ተሰይሞ “1:59:30” እንዲባል ትዕዛዝ ተላልፏል። ፕሬዝዳንቱ ይህ ስኬት በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ ብቻ የሚከሰት ብርቅዬ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸው፣ አትሌቱ ለሀገሩ የሰጠውን ክብር አሞካሽተዋል። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የታርጋ ስያሜ የአትሌቱን ስምና ያስመዘገበውን ክብረ ወሰን ለዘላለም በታሪክ መዝገብ ላይ የሚያኖር ሆኗል።
(አዲስ አድማስ)
More Stories
ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ ሆነ
ፒኤስጂ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!