በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል በሜዳው ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን 0 ለ 0 ተለያይቷል፡፡ አርሰናል የመጀመርያውን ጨዋታ 1 ለ 0 ማሸነፉን ተከትሎ በድምር ውጤት አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍጻሜው አምርቷል፡፡
መድፈኞቹ ለ2ኛ ተከታታይ ዓመት ለግማሽ ፍጻሜ የደረሱ ሲሆን ለፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የሚገናኙ ይሆናል፡፡
በሌላ የሩብ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ባየር ሙኒክ ሪያል ማድሪድን 4 ለ 3 አሸንፏል፡፡ በአሊያንዝ አሬና በደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን፣ ፓቭሎቪች፣ ሉዊስ ዲያዝ እና ሚሼል ኦሊሴ የሙኒክን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
አርዳ ጉለር የማድሪድን ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ ኬሊያን ምባፔ አንድ ግብ አስቆጥሯል፡፡ ሙኒክ የመጀመርያውን ጨዋታ 2 ለ 1 ማሸነፉን ተከትሎ በድምር ውጤት 6 ለ 4 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ መድረሱን አረጋግጧል፡፡
ተቀይሮ የገባው ካማቪንጋ 86ኛው ደቂቃ ላይ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ ከመውጣቱ ሪያል ማድሪድ በተከታታይ ሁለት ግቦች ተቆጥረውበት ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ ሙኒክ በግማሽ ፍጻሜው ከፒኤስጂ የሚጫወት ይሆናል፡፡
More Stories
ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ ሆነ
ፒኤስጂ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን አሸነፈ
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!