April 16, 2026

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ፖርተኞች ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነት በመላበስ ውድድር ማካሄድ እንዳለባቸው የዉድድሩ ስነስርዓት ኮሚቴ ገለፀ።

‎‎በሸካ ዞኑ ስፖርት ምክር ቤት እና በባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አዘጋጅነት የ2018 ዓ.ም እግርኳስ ሻምፒዮና ዉድድር ከሚያዚያ 8 እስከ 16 2018 ዓ.ም በማሻ ከተማ እንደሚካሄድ የዉድድሩ ስነስርዓት ኮሚቴ አስታወቀ ።

‎‎በመድረኩ የዉድድር ደንብ ቀርቦ ዉይይት የተካሄደ ሲሆን ፍፁም ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልክ ውድድሩ ልካሄድ እንደሚገባ ተሳታፊዎች በመድረኩ አንስተዋል ።

‎ለተከታታይ 8 ቀናት በሚካሄደዉ በዚህ ሻምፒዮና 5 ቡድኖች እንደሚሳተፉ የገለፁት የሸካ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጀመረ ተሰማ ዓላማዉ በቅርቡ በሚካሄደው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ዞኑን ወክለዉ የሚሳተፉ ክለቦች የሚለዩበት እንደሆነም ተናግረዋል።

‎ጨዋታዎቹ በዙር የሚደረጉ ሲሆን የዉድድሩ አሸናፍ በነጥብ ይለያል ነው ያሉት።

‎የመክፈቻ ፕሮግራም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በማሻ ሁለገብ ስቴዲየም የሚካሄድ ሲሆን ማሻ ከተማ ከ አንድራቻ ወረዳ የሚገናኙ መሆኑን የድልድሉ መርሃ ግብር ያሳያል ።