የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትግስት ሀሚድ ገለጹ።
በዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር ዙሪያ ያሉ ስጋቶችን ለመፈተሽና መረጃ ላይ የተመሠረተ የመፍትሄ አቅጣጫ ለመቀየስ ያለመ ወርክሾፕ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ትግስት ሀሚድ እንደገለጹት፤ የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።
ወንጀሉ በፋይናንስ ተቋማት፣ በግለሰቦች፣ በሀገር ኢኮኖሚ እንዲሁም በፖለቲካዊና ማህበራዊ ሥነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል ብለዋል።
የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር በዓለም አቀፍ ደረጃ 5 ትሪሊየን ዶላር የሚደርስ ኪሳራ እንደሚያደርስ ጥናቶች እንደሚያመለክቱም በመጠቆም፤ የዲጂታል ፋይናንስ ማጭበርበር ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በጸጥታና ደህንነት አካላት፣ በኢትዮ ቴሌኮም ኦፕሬተሮችና በባንኮች መካከል ያለውን ቅንጅት ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝዋል።
የወንጀሉን ውስብስብነት በመተንተን፣ የሕግ ክፍተቶችን በመለየትና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስልቶችን መንደፍ እንደሚጠበቅም ጨምረው ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ መስፋፋትና የቴሌኮም ዘርፍ መዘመን የማህበረሰቡን የዕለት ተዕለት ግብይት ባህል መቀየሩን እና ባንክ በማይደረስባቸው አካባቢዎች አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና ለሀገር ብልፅግና የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ መሆኑን ገልጸዋል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።