የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ በመሆን ምርትና ምርታማነታቸውን እያሳደጉ መሆናቸውን በሸካ ዞን የየኪ ወረዳ አርሶአደሮች ተናገሩ።
ወቅቱ በሚፈልገው መንገድ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ለበልግ ምርት 10ሺ 5መቶ በላይ የዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ ማቅረቡን የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና የሕብረት ሥራ መምሪያ አስታውቋል።
ያነጋገርናቸው የየኪ ወረዳ አርሶአደሮች እንደተናገሩት መንግስት ባመቻቸላቸው መንገድ የዩሪያ ማዳበሪያ በመጠቀም ምርትና ምርታማነታቸውን እያሳደጉ መሆናቸውን ገልፀው ነገር ግን ከዚህን ቀደም ባለው ዋጋ ላይ ጭማሪ ማሳየቱና የዩሪያ ማዳበሪያ አቅርቦት በቀሌ ደረጃ ያለመሰጠቱ እንቅፋት እንደሆነባቸው ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባሻገር ሁሉም አርሶአደሮች መንግስት ያመቻቸውን ዕድል በመጠቀም በዩሪያ ማዳበሪያ በመዝራት ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠሩ መሆኑን አርሶአደሮቹ ተናግረዋል።
የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አዕምሮ ደሳለኝ እንደገለፁት በበልግ የግብርና ምርት 35ሺ 3መቶ በላይ ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ በእስካሁኑ 25ሺ 2መቶ በማልማት እየተሰራ መሆኑን በመግለፅ 5ሺ8መቶ ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶአደሩ ማቅረብ መቻሉንም ጠቁመዋል።
በዚህም በድንች፣ በቦቆሎ ፣በእንሰት ፣ ምርጥ ዘር በማዘጋጀት 10ሺ 5መቶ በላይ የዩሪያ ማዳበሪያና ዳፕ በዞን ደረጃ ተዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑንም ተናግረዋል።
አክለውም ቀደም ሲል በነበረው ክፍፍል በቀበሌ ደረጃ እንደሚሰራጭ አስታውሰው ይህ አሰራር ለመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠሩ የመንግስት ገንዘብ እንዳይባክን ከማድረግ አኳያ የተደረገ ማሻሻያ መሆኑንም ጠቁመው በኩታ ገጠም በማደራጀት አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
የዋጋ ጭማሪውን በሚመለከት መንግስት በብዙ ብድር የሚያመጣ ምርት በመሆኑ በአለማቀፍ ዋጋ ንረት ምክንያት መሆኑን ህብረተሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባም ተናግረዋል ኃላፊው።
በተጨማሪም አርሶአደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ አቅዶ መስራት እንደማያስፈልግም ተናግረዋል።
የእርሻ ማሳ ዝግጅት በሰዓቱ በማዘጋጀትና የአረም ቁጥጥር ስራ መስራትና ምርት ሳይባክን መስራት እንደሚያስፈልግም አስታውሰዋል።
More Stories
በዓለም ላይ ከፍተኛ ቀውስ እያስከተለ በሚገኘው ጦርነት እስካሁን ምን ተከሰተ?
ኢራን “እራሴን ለመከላከል የምፈጽመውን ጥቃት አጠናክሬ እቀጥላለሁ” አለች
ደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ድርጅት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በቦንጋ ከተማ ተከፈተ