በማስጀመሪያ መረሃ ግብር ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አካልነሽ አየነው የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ጤንነቱ የተገጠበቀ እንዲሆን ክትባቶችን ወቅቱ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው ወላጆችም ልጆቻቸውን እንዲያስከትቡ ጥሪ በማቅረብ ለ5 ዙር የተቀናጀ ክትባት በቴፒ አል ፋሊህ አካዳሚ አስጀምረዋል ።
የቴፒ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ ተሻገር በቀለ በአፍ ጠብታ ለ5ዙር ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከትምህርት ቤት በተጨማሪ ቤት ለቤት ተደራሽ እንደሚሆን የጠቀሙት ኃላፊው በመደበኛ ክትባት መርሃግብር ተደራሽ ያልሆኑ ወይም መጀምረው ያቋረጡ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህፃናትን የመለየትና የመከተብ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግረዋል። ።
በተጓዳኝ የእናቶች ማህፀን ውልቃት(ፈሲቱላ)፣ቆልማማ እግር፣የከንፈር መሰንጠቅ ፣የሥርዓተ ምግብ ችግር ያለባቸውን ህፃናት የመለየትና የህክምና ስራ በተጓዳኝ እንደሚካሄድ ከመረሃ ግብሩ ለማውቅ ተችላል ።።
ከመጋቢት 18 እስከ 21 ድረስ 5ተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት እንደሚካሄድ ታውቋል።
More Stories
ከ 315 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ የምጠበቀው የTELCOM+ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፊዴ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ
በ8 ክልሎች ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ
ዘመቻው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል፦ የክልሉ ጤና ቢሮ