በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሐምሌ 13/2018 ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ቀናት በ52 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚካሄደው የተቀናጀ የጤና ዘመቻ አስፈለጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ገልፅዋል ።
በዘመቻው ከ2.7 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱንም አብራርተዋል።
በዘመቻው ዙሪያ በክልሉ በሁሉም ዞኖች እስከ ቀበሌ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ መፍጠሪያ የጋራ መድረኮች ሲካሄድ መሰንበቱን በማስታወስ፥
ዘመቻው የትራኮማ ምርመራና ህክምና፣ የወባ ምርመራና ህክምና(የአልጋ አጎበር ስርጭት)፣ የኦንኮሰርኪያሲስ በሽታ መከላከያ የመድኃኒት እደላ፣ የማህፀን በር ካንሰር በሽታ ልየታና ህክምና እንዲሁም የቲቢ በሽታ ልየታና ህክምና በምህጻረ ቃል (TELCOM+) ያካተተ እንደሆነም ሀላፊዉ አስረድተዋል።
የተቀናጀ የጤና ዘመቻው በ52 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች 2,765,773 የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ያደርጋል።
ለዘመቻው ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ የባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡም አቶ ኢብራሂም ጥሪ አቅርበዋል።
ክ/መ/ኮ
More Stories
ከ 315 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ የምጠበቀው የTELCOM+ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፊዴ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ
በ8 ክልሎች ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና ምርመራ ዘመቻ ተጀመረ
ዓለምን እያነጋገረ ያለው ‘ሀንታ ቫይረስ’