የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓመተ ምህረት የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ዙሪያ ዉጤታማ የፈተና አስተዳደር ስርዓት እንዲኖር ያለመ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ነዉ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትልና የመማር ማስተማርና ምዘና ዘርፍ ኃላፊ ደስታ ገነሜ (ዶ/ር) የፈተና አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን በባለፉት ጊዜያት በተሰሩት ስራዎች መሻሻሎች መታየታቸውን ገልፀዋል።
በ2017 ትምህርት ዘመን በፈተና አስተዳደር የነበሩ ችግሮች በመገምገም በዘንድሮ ዓመት የተሻለ የፈተና አስተዳር ስርዓት እውን እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል ።
ተማሪዎች በተማሩት ልክ እንዲለኩ ከኩረጃ የፀዳና የዘመነ የፈተና አስተዳደር ስርዓት ድርሻዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል ።
የምዝገባ ሂደት በጊዜ ያለማስከድ ፤በትክክል ያለመመዝገብ እና መሰል ችግሮች በባለፈው ዓመት ፈተና አስተዳደሩ የጋጠሙ ችግሮች መሆናቸዉን ተናግረዉ በዘንድሮ ዓመት በፈተና ስረዓቱ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በትምህርት ስርዓቱ ያለዉን ጉድለት ለመሙላት የፈተና አስተዳደር ስረዓትን ማዘመን ቁልፍ ተግባር መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ደስታ ገነሜ ለዚህም በቴክኖሎጂ የተጋዘ የፈተና አስተዳደር ስርዓት መዘርጋቱን ገልፀዋል።
ተማሪዎች በተማሩት ልክ እንዲለኩ ከኩረጃ የፀዳና የዘመነ የፈተና አስተዳደር ስርዓትን እውን ማድረግ ያስፈልጋል:-ዶ/ር ደስታ ገነሜ
More Stories
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ አዲስ የብልጽግና መንገድ እያሳየች ነው:- ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ለዛምቤዚ ተፋሰስ አገራት ተሞክሮ የሚሆን ነው
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በተፈጠረው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ