ማሻ፤ የካቲት 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ማንችስተር ዩናይትድ ኤቨርተንን 1 ለ 0 ባሸነፈበት ምሽት የግቧ ባለቤት ቤንጃሚን ሼሽኮ ፍጥነት ተጫዋቹ በመልሶ ማጥቃት ምን ያህል አስፈሪ እንደሆነ ማሳያ ሆኗል፡
ዩናይትድ ኳሷን ከራሱ የግብ ክልል ነጥቆ የኤቨርተን መረብ ላይ ለማሳረፍ የፈጀበት ጊዜ 9.2 ሰከንድ ብቻ ሲሆን፣ ይህም የቡድኑን አስደናቂ የሽግግር ፍጥነት ያሳያል።
በተለይ ሼሽኮ ኳሷን ከብሪያን ምቤሞ ተቀብሎ ለማስቆጠር ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል የሮጠበት በሰዓት 35.8 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ያስመዘገበ ሲሆን፣ ይህም በጨዋታው የታየ ፈጣኑ እርምጃ ሆኗል፡፡
ግቧ ከመቆጠሯ በፊት የተደረጉት ቅብብሎች 4 ብቻ መሆናቸው ደግሞ የመልሶ ማጥቃቱ ምን ያህል ቀጥተኛ እና ውጤታማ እንደነበር ማረጋገጫ ነው።
ኳሷ ምንም እንኳን ግብ የመሆን ዕድሏ 0.34 ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ የሼሽኮ ግላዊ ብቃት ግን ይህንን ዝቅተኛ አጋጣሚ ወደ ድንቅ ግብነት ቀይሮታል።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል