ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የነዳጅ ምርት መፈተሻ ላብራቶሪ በድሬዳዋ ከተማ በቅርቡ ልትከፍት መሆኑን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር መዓዛ አበራ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ላብራቶሪው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የነዳጅ ምርቶችና ዘይቶች የተቀመጠውን የጥራት መስፈርት ማሟላታቸውን ለመፈተሽ የሚያስችል ነው።
አገልግሎቱ በቅርበት መሰጠቱ አምራች ድርጅቶችና ተቋማት በተቀላጠፈ መንገድ ጥራት ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ለዚህም ዘመናዊ መሣሪያዎችና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ተቋሙ በድሬዳዋ፣ በአዳማ፣ በሐዋሳና በባሕር ዳር ተጨማሪ የፍተሻ ላብራቶሪዎችን በማደራጀት ላይ እንደሚገኝም ነው ያስገነዘቡት
#ጋዜጣ_ፕላስ
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ