ማሻ፤ የካቲት 11/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ኢትዮ ቴሌኮም ከአገር ውስጥ ገበያ ባለፈ አገልግሎቶቹን በቀጠናው በማስፋፋት ለአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የማበርከት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሳማይላ ዙባይሩ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም የተቋሙን ራዕይና ፍላጎት ጠቅሰው፥ ይህን ዕውን ለማድረግ ጠንካራና የረጅም ጊዜ የፋይናንስ አጋርነት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተቋሙ ከዚህ ቀደም የተገበራቸው ስትራቴጂዎች የተቋሙን ጠንካራ የመፈጸም አቅም በተግባር ያረጋገጡ መሆኑን አስረድተዋል
#አራዳ ኤፍ ኤም
More Stories
የነገ ትውልድ ተስፋ አረንጓዴ ልማትና ቱሪዝም
ህገ ወጥ የቡና ግብይት ቁጥጥርን ማጠናከር እንደሚገባ የካፋ ዞን ምክር ቤት አሳሰበ ።
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ