ማሻ፤ ጥር 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በዘንድሮው አምስተኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባህል ስፖርት ውድደርና የባህል ፌስቲቫል ተሳታፊ የሆነው የሸካ ዞን ታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ቡድን የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
የሸካ ዞን የታዳጊ ወጣቶች እግር ኳስ ቡድን በፍጻሜ ጨዋታው የካፋ ዞን አቻውን 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን የሆነው።
የሸካ ዞን አስተዳደር ባስተላለፈው መልዕክት፣ ይህ ድል የታዳጊ ወጣቶቹን የሜዳ ላይ ብቃት፣ ከፍተኛ ትጋትና የማይበገር የቡድን መንፈስ በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጿል።
ይህ ስኬት የልጆቻችን ውጤት ብቻ ሳይሆን የመላው የሸካ ዞን ህዝብ ኩራት ነው ያለው አስተዳደሩ ለውጤቱ መገኘት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተጫዋቾች፣ አሰልጣኞችና ስፖርት አፍቃሪዎች በሙሉ ምስጋናውን አቅርቧ የዞኑ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ ያሳያል።
በመርሃ ግብሩ ቤንች ሸኮ ዞንን፣ ዳውሮ ዞንንና ምዕራብ ኦሞን በተከታታይ በሰፊ የጎል ልዩነት ያሸነፈው እግር ኳስ ቡድኑ ዞኑ በዘርፉ ያለውን እምቅ አቅም የሚያሳይ ስለመሆኑ አመላካች ነው።
More Stories
የ2026 የካራባኦ ዋንጫ ፍፃሜ …
ሴኔጋል የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮንነቷ እንዲሰረዝ መወሰኑ አሳፋሪ ነው፡- የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኦጉስቲን ሴንግሆር
ቦርንማውዝ ከ ማንችስተር ዩናይትድ