ማሻ፤ ጥር 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ከባህል ስፖርቶች ባሻገር ልዩ ልዩ ስፖርቶችን እንዲሁም የታዳጊ ወጣቶችን ምዘና ማካተቱ የዘንድሮውን ውድድር ለየት ያደርገዋል ያሉት በክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የስፖርት ተሳትፎ እና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በየነ ቴቃ የዘንድሮ ውድድር በሁሉም ዘርፎች የታለመውን ግብ ያሳካ ነበር ብለዋል።
ቀደም ባሉ ጊዜያት ውድድሩ የባህል ስፖርቶች ላይ ያተኩር እንደነበር የጠቀሱት አቶ በየነ ዘንድሮ ግን ለሀገር ብሎም ለዓለም ተወዳዳሪ ልሆኑ የሚችሉ ታዳጊዎችን ለመለየት የሚያስችል አጋጣሚ የተፈጠረበት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በተለይ የታዳጊዎች ውድድር የጠቅላይ ሚኒስትር ኢንሼቲቭ ከመሆኑም ባሻገር ክልሉን የሚወክሉ ታዳጊ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል በመሆኑ ዕድሜ የመለየት ጉዳይ ትኩረት የተሰጠበት እንደነበርም ተናግረዋል።
በዚህም የዚህ ዙር ተሳታፊዎች ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 15 ብቻ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ይህም ውጤታማ ልየታ የተደረገበት እንደነበርም ገልጸዋል።
ከስፖርት ውድድር ባሻገር የየዞኖች የባህል ቡድን አባላት ባህሎቻቸውን ለማስተዋወቅ ያደረጉት ጥረት ለባህል ዲፕሎማሲ ዕድገት ዕድል የፈጠረ እንደነበር አቶ በየነ ከሚዲያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
More Stories
ኢትዮጵያዊ በዳምጠው ከበደ ተጨማሪ ሜዳሊያ አገኘች
ቴፒ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
የኤሲሚላን የቀድሞ ተጫዋች ፍራንኮ ባሬዚ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ