ማሻ፤ ጥር 12/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8)በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ7ኛ ዙር መርሐ ግብር ከሜዳው ውጭ የኖርዌዩን ቦዶ ግሊምት የገጠመው ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
ካስፐር ሆግ (2) እንዲሁም ጄንስ ሀውጅ ባስቆጠሯቸው ግቦች በቦዶ ግሊምት 3 ለ 0 ሲመሩ የቆዩት ሲቲዎች በባዶ ከመሸነፍ የዳኑበትን ብቸኛ ግብ ራያን ሼርኪ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በማንቼስተር ሲቲ በኩል አማካዩ ሮድሪ በሁለት ቢጫ ካርድ 62ኛው ደቂቃ ላይ ከሜዳ ተሰናብቷል።
ቀደም ብሎ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 በተደረገው የዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ክለብ ብሩጅ ካይራት አልማቲን 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የሻምፒየንስ ሊጉ የ7ኛ ዙር መርሐ ግብር ቀጥለው ሲደረጉ በመድረኩ በዚህ የውድድር ዓመት በብቸኝነት ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አርሰናል ምሽት 5 ሰዓት ኢንተር ሚላንን ይገጥማል።
ሪያል ማድሪድ ከሞናኮ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከፒኤስጂ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር ከቦሩሺያ ዶርትመንድ፣ ቪያሪያል ከአያክስ አምስተርዳም እንዲሁም ኦሎምፒያኮስ ከባየር ሊቨርኩሰን በተመሳሳይ 5 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል