ማሻ፤ ጥር 15/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውድድር በዛሬው ዕለት የተለያዩ የባህላዊ፤ ፓራ ኦሎምፒክና የታዳጊ ወጣቶች አትሌትክስ ውድድር ተካሂደዋል።
በባህላዊ ስፖርታዊ ውድድሮች በገበጣ ወንድ ካፋ ከኮንታ ጋር በተደረገው ፉክክር ዳውሮ 2ለ0 ኮንታን አሸንፈዋል። ቡብ በወንድ ካፋ ከዳውሮ ጋር በተደረገው ውድድር ካፋ ዳውሮን 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።ሻህ በሴት ኮንታና ዳውሮ መካከል በተደረገው ውድድር ዳውሮ ኮንታን 2ለ0 አሸንፈዋል። ገበጣ ባለ 12 ወንድ ቤንች ሸኮና ምዕራብ ኦሞ መካከል በተደረገው ውድድር ምዕራብ ኦሞ ቤንች ሸኮን 2ለ0 መርታት ችለዋል።በተመሳሳይ ገበጣ ባለ 18 ሴት ኮንታ ከዳውሮ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ኮንታ 2ለ0 ዳውሮን አሸንፏል።በሻህ ወንድ ዳውሮ ከካፋ ጋር ባደረጉት ውድድር ካፋ ዳውሮን 2ለ0 አሸንፏል።
ከባህላዊ ውድድሮች በተጨማሪ የተለያዩ አትሌትክስ ውድድሮች የተደረጉ ስሆን 100 ሜትርና 800 ሜትር ሴቶች ፍፃመውን አግኝተዋል።
ዛሬ በተደረገው የታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ ማጣሪያ ጨዋታ ካፋ ዳውሮ ጋር በተደረገው ውድድር ካፋ 2ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።
የውድድሩ አንድ አካል በሆነው ፓራ ኦሎምፒክ ውድድር በጦርና በአሎሎ ውርወራ የፍፃሜ ውድድር ተካሂደዋል።
ውድድሩ እስከ ጥር 19 ተጠናክሮ የሚቀጥል ስሆን ነገ በሚኖረው ውድድር የተለያዩ የፍፃሜና የደረጃ ውድድሮች እንደሚካሄድ ከመርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል። ዘገባው የክልሉ መ/ኮ ነው።
ዛሬ በተካሄደው 5ኛ ዙር ክልል አቀፍ የባህል ስፖርቶች የባህል ፌስትቫልና የታዳጊ ወጣቶች ሚዘርና የተለያዩ የፍፃሜና የማጣሪያ ጨዋታዎች ተካሂደዋል።
More Stories
የሸካ ዞን የታዳጊ ወጣቶች የእግርኳስ ቡድን የ2018 ክልል አቀፍ ውድድር የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።
5ተኛው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የባህል ስፖርቶች ውድድር፣ የባህል ፌስቲቫል እና የታዳጊ ወጣቶች ምዘና ውድድር የታለመውን ግብ ያሳካ መሆኑ ተገለጸ።
ባካሪ ሳኛ ኢትዮጵያ ገባ