ማሻ፣ ጥር 03/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) አሜሪካ በሶሪያ በሚገኘው እስላማዊ መንግስት ብላ በምትጠራው ላይ ከባድ ጥቃት ፈፀመች ተባለ።
ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ወር በሶሪያ ፓልሜራ በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ለደረሰው ጉዳት የበቀል ምላሽ ነው ስትል ዋሽንግተን አስታውቃለች።
የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ እንዳስታወቀው ፣ አይ አይ ኤስ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት አድርሷል።
ዘመቻ ሀውክአይ በተሰኘው ትራምፕ መራሽ ጥቃት አይ ኤስ ሲጠቀምበት የነበረው የጦር መሳሪያ መውደሙን ማዕከላዊ ዕዙ አክሎ ገልጿል።
አይ ኤስ ላይ የተወሰደው እርምጃ ለወደፊቱ ቡድኑ ለሚያደርገው ጥቃት ከባድ አጸፋ እንደሚጠብቀው ለማስጠንቀቅ ነው ሲሉ የዋሽንግተን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በአሜሪካ ጦር እና ተባባሪዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት መልሱ የከፋ መሆኑን አይ ኤስ እና ሌሎች ቡድኖች ማወቅ አለባቸው ሲል ማዕከላዊ ዕዙ በኤክስ ገፁ ላይም አስፍራሯል ሲል ታይምስ ኦፍ ኢንዲያን ጠቅሶ ኤን ቢሲ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ