ማሻ፣ ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ሱዳን ኢኳቶሪያል ጊኒን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በሞሮኮ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ምሽት 12፡00 ላይ በተደረገው ጨዋታ የሱዳንን የማሸነፊያ ግብ ሳውል ኮኮ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏል።
ቀደም ሲል ቀን 9፡30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ሞዛንቢክ ጋቦንን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችላለች።
የዕለቱ መርሐ ግብር ቀጥለው ሲካሄዱ ምሽት 2:30 ላይ አልጄሪያ ከቡርኪናፋሶ፤ ምሽት 5 ሰዓት ኮቲዲቯር ከካሜሩን ይጫወታሉ።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል