ማሻ፣ ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም (ማሻ ኤፍኤም 103.8) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ቀን 9 ሰዓት ከ30 ኖቲንግሃም ፎረስት በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ ላይ የተቀመጠውን ማንቼስተር ሲቲን ያስተናግዳል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ደግሞ የሊጉ መሪ አርሰናል በሜዳው ከብራይተን ጋር ሲጫወት ሊቨርፑል በተመሳሳይ ሰዓት በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን ዎልቭስን ያስተናግዳል፡፡
ብረንትፎርድ ከቦርንማውዝ፣ በርንሌይ ከኤቨርተን እንዲሁም ዌስትሃም ከፉልሃም በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።
ምሽት 2 ከ30 ላይ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ በሊጉ ሶስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠውን አስቶንቪላ የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 18ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ትናንት ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሲጀምር በሜዳው ኦልድትራፎርድ ኒውካስልን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወቃል።
More Stories
አርሰናል 5 ተጨዋቾችን ያስመረጠበት የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ 11 ይፋ ተደረገ
ብሩኖ ፈርናንዴዝ የፒ ኤፍ ኤ የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን አሸነፈ
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ ማጣሪያ ቅድመ ዝግጅቱን ዛሬ ይጀምራል