ማሻ፣ ታህሳስ 15/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም 103.8) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (የፈረንጆች ገና) በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
የገና በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን በማሰብ የሚከበር ሲሆን ÷ በመላው ዓለም የሚገኙ የበዓሉ አክባሪዎች የተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችን ያከናውናሉ።
በዓሉን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ ሜክሲኮ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፖላንድ፣ ስፔን፣ ኖርዌይ እና ብራዚልን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት በዛሬው ዕለት እያከበሩ ይገኛል፡፡
በአፍሪካም ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ታንዛኒያ እና ኬንያን ጨምሮ ከ40 በላይ የሚሆኑ ሀገራት የገና በዓልን በድምቀት በማክበር ላይ ናቸው፡፡
በበርካታ ሀገራት የገና በዓል ዝግጅት የሚጀመረው ከዋዜማው ቀደም ብሎ ሲሆን ÷ የበዓሉ ቀን ደግሞ በልዩ ዝግጅቶቸ እንዲሁም የቤተሰብ አባላት በመሰባሰብ አንድ ላይ ያከብራሉ።
ከበዓሉ ቀደም ብሎ ጎዳናዎች፣ አደባባዮች፣ ሕንጻዎችና መኖሪያ ቤቶች የተለያየ ዲዛይን ባላቸው መብራቶች እና ጌጣጌጦች ያሸበርቃሉ፡፡
የበዓሉ አክባሪዎች ልዩ ልዩ ስጦታዎችን፣ የመልካም ምኞት መግለጫ ካርዶችን እና መልዕክቶችን በመለዋወጥ በዓሉን በደስታ ያሳልፋሉ፡፡
የገና በዓልን በፈረንጆቹ ታሕሣሥ 25 የሚያከብሩ ሀገራት የግሪጎሪያን አቆጣጠር የሚጠቀሙ ሲሆን÷ በፈረንጆቹ ጥር 7 በዓሉን የሚያከብሩት ደግሞ የጁሊያን የቀን መቁጠሪያ የሚከተሉ ሀገራት ናቸው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራትም የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል ታሕሣሥ 29 ቀን ያከብራሉ።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።