ማሻ ፣ የታሕሳስ 17/04/2018 (ማሻ ኤፍ ኤም)በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተማ አቀፍ የህዝብ ውይይት መድረክ መካሄድ ጀምረዋል ።
በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው የጋራ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ ሀገራችን ከለውጥ በፊት ያጋጠማትን የማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለትካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስብራት ለመጠገን መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ውጤታማ ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
“የጉባ ብስራቶች ፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል የህዝቡን ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ዕውን ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ በመሆኑ የጉባ ብስራቶችና የመደመር መንግስት ትሩፋቶች ላይ በህዝብና በመንግስት ቅንጅት የመጣው ለውጥ የሀገራችን ከፍታ ያሳየ ነው ብለዋል።
በውይይቱ ላይ በህዝብና መንግስት ቅንጅት የመጡ ለውጦችንና ስኬቶችን በመገምገም ጠንካራ ጎን በማስቀጠል ድክመቶችን በማረም በጉባ ብስራቶች የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በማስቀጠል ውጤታማ ለውጥ ማስመዝገብ የምንችልበትን አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ነው ብለዋል።
በመደመር መንግስት ትሩፋቶች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በግብርና ውጤቶች ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት ላይ መሆኑን በመግለፅ ምርትና ምርታማነትን አሁንም በተለያዩ የግብርና ስራዎች በማምጣት የተሻለ ለውጥ ማስመዝገብ ላይ የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን ማስቀጠል አለብን ብለዋል።
በዚህ የህዝብ ውይይት መድረክ ላይ ከ4መቶ በላይ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት የተወጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች፣ወጣቶች፣ሴቶች ፣ታዋቂ ግለሰቦች ፣ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣የከተማ መንግስት ሰራተኞችና ለሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
More Stories
ዜጎች በመልዕክት መላላኪያ አማራጮች በሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ተጋላጭ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡-የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
በሸካ ዞን አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ እና የህግ የበላይነትን ለማስከበር ያለመ ዞናዊ የፀጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ በቴፒ ከተማ ተካሄደ
ክልላዊ የተቀናጀ የማኅበረሰብ አቀፍ ተፋሰስ ልማት ማብሰሪያ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።