ይህ የተገለፁው የሸካ ዞን ግብርና፣ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ ልማት መምሪያ የአውሮፓ ህብረት ከደን ጭፍጨፋ ነፃ ምርት አቅርቦት (EUDR) ደንብና በቡና ማሳ Geo location Data አሰባሰብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ባለበት ወቅት ነው ።
በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ እየተሰጠ ባለው በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉ የግብርና ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት ቡናን ጨምሮ ሌሎች በአውሮፓ ሀገራት የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች ከደን ጭፍጨፋ ነፃ ሆነው እንዲመረቱ ከማድረግ እንፃር በትኩረት እንሰራለን ብለዋል ።
ከስልጠናው የተሻለ ግንዛቤ እያገኙ መሆናቸውን የተናገሩት የግብርና ባለሙያዎች በሰለጠኑት ልክ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ስለመሆናቸውም አክለዋል ።
ሰልጣኞቹ ከስልጠናው ጎን ለጎን በሸካ ዞን የኪ ወረዳ አዲስ ብርሃን ቀበሌ በተመረጡ የቡና ማሳዎች ላይ በሰለጠኑት አግባብ የተግባር ልምምድ አድርገዋል ።
እየተሰጠ በሚገኘው በዚህ ስልጠና ላይ የማሻ ወረዳ ፣ የየኪ ወረዳና የአንድራቻ ወረዳ ግብርና ፅ/ቤት ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የተለያዩ የልማት ጣቢያ ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ – አስቻለው አየለ
More Stories
እየተጠናከረ የመጣው የብሪክስ ሀገራት ግንኙነት…
አሜሪካ ሶሪያን አጠቃች
የሩሲያ ጦር በፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ ተፈጽሟል ላለው ጥቃት አፀፋ በዩክሬን ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል።