ማሻ ፣ የሰኔ 23፣ 2017 (ማሻ ኤፍ ኤም) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ የዜና ጣብያ ጋር ባደረጉት ቆይታ የአጫጭር ቪዲዮ ማጋሪያ የሆነውን ቲክ ቶክ የሚገዙ ባለሀብቶች ማግኘታቸውን አስታዉቀዋል።
የገዢዎቹን ማንነት ከሁለት ሳምንት በኋላ ይፋ እንደሚያደርጉም ነው ፕሬዝዳንቱ የገለፁት።
ንግግሩ አሁን ላይ እየተደረገ መሆኑንና ከቻይና ፈቃድ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፤ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ያደረጉታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
ባለፈው ዓመት ባይትዳንስ የተሰኘው የቻይናው ኩባንያ የቲክቶክ መተግበሪያን ለአሜሪካዊ ባለሃብት የማይሸጥ ከሆነ እንዲዘጋ መወሰኑ ይታወሳል።
ሆኖም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ስልጣን በመጡ ጊዜ ሊዘጋ የነበረውን ቲክ ቶክን በ3 ወር አራዝመው ለአሜሪካዊ ድርጅት እንዲሸጥ ጥሪ አቅርበው ነበር።
አሁን ላይ ገዢ እንደተገኘ እና ንግግር ላይ መሆናቸውን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ፤ በሚቀጥሉት ሳምንታት የገዢዎቹን ማንነት በይፈ እንደሚያስታውቁ ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቅርቡ ቲክቶክ ለተጨማሪ 90 ቀናት በሀገረ አሜሪካ እንዲሰራ መፍቀዳቸዉ የሚታወስ ነዉ።
ኢቢሲ
More Stories
ሩሲያ እና ህንድ በጦር መሳሪያ አቅርቦት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ እንደሚሰሩ አስታወቁ፡፡
ኢራን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉባት የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ቁጥር 10 ደረሰ
ትራምፕ የቡድን 7 ጉባዔ ሳይጠናቀቅ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ