በ16 ተሽከርካሪ ወደ መሀል ሀገር ሊገቡ የተዘጋጁ 525 ሚሊየን 245 ሺህ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በትናንትናው ዕለት በሶማሌ ክልል ቢዮባሃይ በተባለ አካባቢ ተያዙ፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ ሊያዙ የቻሉት የሶማሌ ክልል መንግሥት የፀጥታ አካላት፣ የሀገር መከላከያ እና የፌደራል ፖሊስ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከልም አልባሳት፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ መድኃኒት፣ ሲጋራ፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የክትትል ሥራዎች ተጠናክረው መቀጣላቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
EBC
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ