የፈረንሳዩ እግር ኳስ ክለብ ፒኤስጂ አርሰናልን በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በድጋሚ አንስቷል፡፡
ፒኤስጂ ከአስቸጋሪ አጀማመር በኋላ አርሰናልን በመለያ ምት 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በመርታት ነው ለ2ኛ ተከታታይ ዓመት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሳካት የቻለው፡፡
ጨዋታው በጀመረ በ6ኛው ደቂቃ ካይ ሃቨርትዝ ለአርሰናል የመሪነቷን ግብ አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በአርሰናል 1 ለ 0 መሪነት ተጠናቅቋል፡፡
ይሁን እንጂ በሁለተኛው አጋማሽ ፒኤስጂ በ65ኛው ደቂቃ በኡስማን ዴምቤሌ የፍጹም ቅጣት ምት ግብ አቻ ሆኗል።
መደበኛ የጨዋታ ጊዜው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎም ጨዋታው ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ያመራ ሲሆን፥ በዚህም ሳይሸናነፉ ቀርተዋል።
በመጨረሻም ፒኤስጂ አርሰናልን በመለያ ምት 4 ለ 3 በማሸነፍ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን በድጋሚ ማንሳት ችሏል።
More Stories
ሪያል ማድሪድ የዓለማችን ውዱ ክለብ ሆነ
ክሪስታል ፓላስ የአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ሻምፒዮን ሆነ!
ኢትዮጵያ ከዓለም ዋንጫው ውጪ ሆነች