የሳይንስ ልብ ወለድ ፊልሞች እውን እየሆኑ ነው። ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ የሚመራው ኒውራሊንክ (Neuralink) የተባለው ተቋም፣ እጅግ ረቂቅ የሆኑ የቺፕ ክሮችን በቀዶ ጥገና ወደ ሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ ማስገባት የሚችል አስገራሚ ሮቦት ይፋ አድርጓል።
ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ መራመድ ለማይችሉ፣ የማየት ችግር ላለባቸው እና በተለያዩ የአእምሮ ህመሞች ለሚሰቃዩ ወገኖች አዲስ ተስፋ ይዞ ብቅ ብሏል።
ይህ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተገጠመለት የሮቦት ሥርዓት፣ ከሰው ጸጉር እጅግ የቀጠኑ የኤሌክትሮድ ክሮችን ወደ አእምሮ ክፍል ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ ያሰርጋል።
የቀዶ ጥገናው ሂደት እጅግ ረቂቅ ከመሆኑ የተነሳ የሰው ልጅ እጅ ሊሰራው የማይችለውን ትክክለኛነት ይጠይቃል። ሮቦቱ የተገጠሙለትን ካሜራዎች እና የሴንሰር መቆጣጠሪያዎች በመጠቀም በአይን እና በልብ ትርታ ምክንያት በአንጎል ውስጥ የሚፈጠሩ ጥቃቅን እንቅስቃሴዎችን በቅጽበት እያጠና እራሱን ከአንጎሉ መዋቅር ጋር ማስተካከል ይችላል ነው የተባለው።
ቴክኖሎጂው ቀደም ሲል ከነበሩት የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ብቻ ከሚቆጣጠሩ የአንጎል መትከያዎች በተለየ መልኩ፣ አሁን የሰው ልጅን የንግግር ችሎታ፣ የማስታወስ አቅም፣ የስሜት መለዋወጥን እና የእይታ ማዕከላትን በቀጥታ ማገናኘት የሚያስችል አቅም አለው።
ይህም እንደ ፓርኪንሰን፣ የሚጥል በሽታ እና የአከርካሪ አጥንት ጉዳት ያሉ ከባድ የነርቭ ችግሮችን ለመፍታት ትልቅ በር ይከፍታል።
ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂው በሙከራና በምርምር ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም፣ የሰው ልጅን የማሰብ አቅም ከዲጂታል ዓለም ጋር የማስተሳሰሩ ህልም ከምንጊዜውም በላይ ወደ እውነታው እየተቃረበ መሆኑን ያሳያል።
More Stories
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ
በብልፅግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ያደሩ በርካታ የልማት ጥያቄዎችን ከመፍታት ባሻገር አዳዲሶቹን ጀምሮ በማጠናቀቅ የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ አቶ ፍቅሬ አማን ገለጹ።