አሜሪካ የ108 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የዩክሬንን አየር መከላከያ ሥርዓት የሚያጠናክሩ እና ተያያዥ የድጋፍ መሳሪያዎችን ለመሸጥ አጸደቀች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው÷ የወታደራዊ ቁሳቁስ ሽያጩ ኤችኤደብሊውኬ (HAWK) የተባለውን የዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት የሚደግፍ ነው።
ስምምነቱ የጥገና፣ የመለዋወጫ እቃዎች፣ የምህንድስና እና የሎጂስቲክስ ድጋፍን ያካተተ መሆኑን ገልጿል።
ይህም የዩክሬንን የአየር መከላከል አቅምን ያጠናክራል መባሉን ኬይቭ ፖስት ዘግቧል።
እንዲሁም ሀገሪቱ ራሷን ለመከላከልና ለቀጣናው ደኅንነት ተልዕኮዎች ያላትን የተቀናጀ የአየር መከላከያ አቅም በማጠናከር ወቅታዊ እና የወደፊት ስጋቶቿን ለመፍታት እንደሚረዳ ተገልጿል።
More Stories
በቴፒ ከተማ ተቋቁሞ አገልግሎት እየሰጠ ያለው የመሶብ አንድ ማዕከል ከእንግልትና ከምልልስ እንደታደጋቸው ተገልጋዮች ተናገሩ
ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፡- በብዝኃነት ላይ የተመሠረተ ወል ትርክትን የመገንባት ጉዞ
የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ስራ ስኬታማነት ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ተባለ